PIONEER IN THE PHARMACEUTICAL MANUFACTURING SINCE 1964

የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር በማምረት ላይ ይገኛል

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) (COVID-19) በቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ህመም   የሚያስከትል ቫይረስ ነው ፡፡በሽታው ከቀን ወደ ቀን ሊባባስ እና እንደ ሳንባ ምች (pneumonia) ከባድ የመተንፈሻ ህመም ብሎም የኩላሊት ስራ ማቆምና ሞትን ሊያስከትል የሚችል እና በአለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኝ በሽታ ነው፡፡

COVID-19 በሽታ ያለባቸዉ ሰዎች ከመጠነኛ እስከ ከባድ የመተንፈሻ ህመም ጨምሮ  ትኩሳት፣ ደረቅ ሳል  እና የትንፋሽ እጥረት  የጉሮሮ ህመም ዋነኞቹ ምልክቶቹ ሲሆኑ ከበሽታ ክብደት አንፃር መከላከል ዋነኛው አመራጭ ነው ፡፡  የመከላከያ ዘዴዎቹ ደግሞ በተደጋጋሚ እጅን በሳሙና እና በዉሃ መታጠብ ውሃ እና ሳሙና በማያገኙበት ቦታ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር  መጠቀም፣ሲያስሉ አፍና አፍንጫን በክርን  ሸፍኖ ማሳል፣ማህበራዊ ፈቀቅታን መተግበር ፣በተደጋጋሚ የሚነኩ እቃዎችንና ገፅታዎች በ አልኮል ባላቸው ማፅጃዎች ማፅዳትና ተዋስን ማስወገድ ይኖርብናል ።

በአሁኑ ሰዓት የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት በመስፋፋት በርካታ የዓለም ሀገራት እያስጨነቀ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ መንግስታት ያላቸው አቅም ሁሉ ተጠቅመው  የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ  ፡፡    በሃገራችን ኢትዮጵያም ቫይረሱ በተወሰኑ ሰዎች ላይ መገኘቱን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የጤና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳይፈጠር መንግስትና የሚመለከታቸው ተቋማት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ ፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን  የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ  የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚጠቅም የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር  WHO recommended hand rub solution (sanitizer ) በማምረት ካለበት ሃገራዊ እና  ማኅበራዊ ሃላፊነት  አንፃር   ከሚያገኘወ ገቢ 20% የሚሆነውን   ለአረጋውያን እና ለአእምሮ ህሙማን መንከባከቢያዎች ማረሚያ ቤቶች መቄዶንያ  የአረጋውያን ለአእምሮ ህሙማን መንከባከቢያ ፣ ለጌርጌሶን የአረጋውያን ለአእምሮ ህሙማን መንከባከቢያ ፣ለስሊዮንየ አረጋውያን ለአእምሮ ህሙማን መንከባከቢያ ለቂሊንጦ ማረምያ ቤቶች እና ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራያዊ ሪፐብሊክ የሰላም ሚኒስቴር  በነፃ እየሰጠ ይገኛል ፡፡

በቀጣይም የአፍ እና የአፍንጫ  መሸፈኛ ጭንብሎችን ለማምረት አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ በቅርቡ ማምረት ይጀምራል ፡፡

 

 

 

                           

                             

 

 

                             

 

epharm

About epharm