የኢ.መ.ፋ ሳኒታይዘር እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ምርቶች የምረቃ ስነ ስርዓት
የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ አ.ማ ያመረታቸውን የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘሮችን እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ነሃሴ 9/ 2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጤና ሚኒሰቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና የንግድ እና ኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በተገኙበት በይፋ አስመረቀ፡፡በዝግጅቱ ላይም ኮቪድ -19ን ለመከላከል ግንባር ቀደም ተሳታፊ ለሆኑት የህክምና ባለሙያዎች 100,000 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን ቃል በገባው መሰረትም ነሃሴ 14/ 2012 የኢትዮጵያ ጤና ሚንስቴር ቢሮ በመገኘት የኢትዮጵያ ጤና ሚንስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በተገኙበት በኢ.መ.ፋ ቦርድ ሰብሳቢ በዶ/ር መሀመድ ኑሪ አመካኝነት ማስረከቡን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡